የመልካም መንገድ ዓለም አቀፍ የተልእኮ አገልግሎት

ስለ እኛ

የመልካም መንገድ ዓለም አቀፍ የተልእኮ አገልግሎት የእግዚአብሔርን ቃል እውነት ለሰዎች ሁሉ ለማድረስ፣ ወደ ክርስቶስ ለመምራት፣ ጠንካራ ደቀ መዛሙርትን ለማሳደግ እና የእግዚአብሔርን መንግሥት በትውልድ ሁሉ ለማስፋፋት የቆመ አገልግሎት ነው።

ራእያችን

የእግዚአብሔር ቃል በዓለም ሁሉ እንዲደርስ፣ ሰዎች ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ፣ ጠንካራ ደቀ መዛሙርት እንዲነሱ እና የእግዚአብሔር መንግሥት በትውልድ ሁሉ እንዲስፋፋ ማየት።

እንዲሁም በክርስቶስ ፍቅር የተመሠረተ አንድነት፣ ተስፋና ሕይወት የሞላበት፣ ለክርስቶስ ወንጌል የጨከነ ትውልድ መነሳትን ማየት።

ተልእኮአችን

  • የእግዚአብሔርን ቃል በታማኝነት መስበክና ማስተማር፤ ወንጌልን ለሰዎች ሁሉ በእውነትና በፍቅር ማሰራጨት።
  • ሰዎችን ወደ ድነት መንገድ መምራት፤ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ግላዊ ግንኙነት እንዲኖራቸውና አዲስ ሕይወትን እንዲለማመዱ መርዳት።
  • በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ በጸሎትና በመንፈሳዊ ምክር ጠንካራ ደቀ መዛሙርትን መገንባት።
  • አገልጋዮችንና አብያተ ክርስቲያናትን በስልጠና፣ በግብዓቶች፣ በድጋፍ እና በስኮላርሺፕ ማብቃት።
  • በወንጌል ምክንያት ለስደት የሚጋለጡትን ማበረታታትና ዘላቂ መፍትሄ መስጠት፤ መጠለያ፣ ምግብና የሙያ ስልጠና ማመቻቸት።
  • በክርስቶስ አካል ውስጥ ፍቅርን፣ አንድነትንና ትብብርን ማበረታታት።
  • ወንጌል ባልደረሰባቸው አካባቢዎች ሚስዮናውያንን መላክና አብያተ ክርስቲያናት እንዲተከሉ ማድረግ።
  • የመንግሥቱን ራእይ ማስፋፋት፤ መሪዎችን ማሳደግና የመልካም መንገድን ራእይ የሚያራምዱ አገልግሎቶችን ማቋቋም።

ዋና እሴቶቻችን

በእግዚአብሔር ቃል እውነት መመራትና በታማኝነት መኖር።

ሁሉን በክርስቶስ ፍቅር መቀበልና ማገልገል።

በሁሉም ነገር እውነተኛና ታማኝ መሆን።

ራስን ዝቅ አድርጎ ሌሎችን በትሕትና ማገልገል።

በክርስቶስ አካል ውስጥ አንድነትንና ትብብርን ማጠንከር።

ሁሉን በጸሎት መጀመርና በእግዚአብሔር ማመን።

ለእግዚአብሔር ፈቃድ ታዛዥ መሆን።

ለደካሞችና ለተቸገሩ ርኅራኄ ማሳየት።

በአገልግሎት ሁሉ በጥራትና በትጋት መሥራት።

የእምነት መግለጫ

በአንዱ እውነተኛ አምላክ — በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን፤ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ፣ ለድነታችን በሞቱና በትንሣኤው እናምናለን፤ በቅዱሳት መጻሕፍት ሥልጣን እና መላው ቤተ ክርስቲያን ሕዝቦችን ሁሉ ደቀ መዛሙርት እንድታደርግ በተጠራችው ጥሪ እናምናለን። (ሙሉ የእምነት መግለጫ ይጨመራል።)

አመራር

የአመራር ቡድናችን በቅርቡ እዚህ ይተዋወቃል።