የመልካም መንገድ ዓለም አቀፍ የተልእኮ አገልግሎት

የመልካም መንገድ ዓለም አቀፍ የተልእኮ አገልግሎት

ወንጌልን በታማኝነት እያሰራጨን ሰዎችን ከክርስቶስ ጋር ወደ አዲስ ሕይወት እንመራለን።

የእግዚአብሔርን ቃል በእውነትና በፍቅር እንሰብካለን፤ ደቀ መዛሙርትን እናፈራለን፤ አገልጋዮችንና አብያተ ክርስቲያናትን እናስታጥቃለን፤ ለተሰደዱም ጎን እንቆማለን — በኢትዮጵያና ከዚያ ባሻገር።

“ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።”

ማርቆስ 16:15

አገልግሎቶቻችን

ተልእኮአችን

የእግዚአብሔርን ቃል በታማኝነት መስበክና ማስተማር፣ ሰዎችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ድነት መምራት፣ ጠንካራ ደቀ መዛሙርትንና ጤናማ አብያተ ክርስቲያናትን መገንባት።

  • የእግዚአብሔርን ቃል በታማኝነት መስበክና ማስተማር፤ ወንጌልን ለሰዎች ሁሉ በእውነትና በፍቅር ማሰራጨት።
  • ሰዎችን ወደ ድነት መንገድ መምራት፤ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ግላዊ ግንኙነት እንዲኖራቸውና አዲስ ሕይወትን እንዲለማመዱ መርዳት።
  • በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ በጸሎትና በመንፈሳዊ ምክር ጠንካራ ደቀ መዛሙርትን መገንባት።
  • አገልጋዮችንና አብያተ ክርስቲያናትን በስልጠና፣ በግብዓቶች፣ በድጋፍ እና በስኮላርሺፕ ማብቃት።
  • በወንጌል ምክንያት ለስደት የሚጋለጡትን ማበረታታትና ዘላቂ መፍትሄ መስጠት፤ መጠለያ፣ ምግብና የሙያ ስልጠና ማመቻቸት።
  • በክርስቶስ አካል ውስጥ ፍቅርን፣ አንድነትንና ትብብርን ማበረታታት።
  • ወንጌል ባልደረሰባቸው አካባቢዎች ሚስዮናውያንን መላክና አብያተ ክርስቲያናት እንዲተከሉ ማድረግ።
  • የመንግሥቱን ራእይ ማስፋፋት፤ መሪዎችን ማሳደግና የመልካም መንገድን ራእይ የሚያራምዱ አገልግሎቶችን ማቋቋም።

የምናደርገው

በቅዱስ ቃል ላይ የተመሠረቱ ስምንት የአገልግሎት መስኮች፤ በእነዚህም የክርስቶስን አካል እናገለግላለን፤ የጠፉትንም እንፈልጋለን።

የእግዚአብሔርን ቃል መስበክና ማስተማር

የእግዚአብሔርን ቃል በታማኝነት እንሰብካለን፤ እናስተምራለን፤ ወንጌልንም ለሰዎች ሁሉ በግልጽነት፣ በእውነትና በፍቅር እናሰራጫለን።

ማርቆስ 16:15

ሰዎችን ወደ ድነት መምራት

ሰዎችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግላዊ ግንኙነት እንመራለን፤ ድነትን፣ ለውጥንና አዲስ ሕይወትን እንዲለማመዱ እንረዳለን።

ደቀ መዝሙርነት

አማኞች መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያገኙ ትኩረት በመስጠት፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ በጸሎትና በመንፈሳዊ ምክር ጠንካራ ደቀ መዛሙርትን እንገነባለን።

ማቴዎስ 28:19

አገልጋዮችንና አብያተ ክርስቲያናትን ማስታጠቅ

አገልጋዮችና አብያተ ክርስቲያናት በጥሪአቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ስልጠና፣ ግብዓቶችና ድጋፍ እንዲሁም ስኮላርሺፕ በመስጠት እናበቃቸዋለን።

ኤፌሶን 4:12

የአገልጋዮች እንክብካቤ

በአገልግሎት ላይ ያሉ አገልጋዮችን ድጋፍ በሚያስፈልጋቸው ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ቀርበን በማነጋገር ተገቢ የሆኑ ድጋፎችን እናደርጋለን።

ለተሰደዱ ጎን መቆም

በወንጌል ምክንያት ለስደትና ለችግር የሚጋለጡ ወንድሞችንና እህቶችን እናበረታለን፤ የሙያ ስልጠናና ስኮላርሺፕ በማመቻቸት ራሳቸውን እስኪችሉ ድረስ መጠለያና ምግብ የሚያገኙበትን ስፍራ እናዘጋጃለን።

ዕብራውያን 13:3

ራእያችን

የእግዚአብሔር ቃል በዓለም ሁሉ እንዲደርስ፣ ሰዎች ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ፣ ጠንካራ ደቀ መዛሙርት እንዲነሱ እና የእግዚአብሔር መንግሥት በትውልድ ሁሉ እንዲስፋፋ ማየት።

እንዲሁም በክርስቶስ ፍቅር የተመሠረተ አንድነት፣ ተስፋና ሕይወት የሞላበት፣ ለክርስቶስ ወንጌል የጨከነ ትውልድ መነሳትን ማየት።

ዋና እሴቶቻችን

የምናደርገውን ሁሉ የሚመሩ መሠረታዊ እምነቶቻችን።

በእግዚአብሔር ቃል እውነት መመራትና በታማኝነት መኖር።

ሁሉን በክርስቶስ ፍቅር መቀበልና ማገልገል።

በሁሉም ነገር እውነተኛና ታማኝ መሆን።

ራስን ዝቅ አድርጎ ሌሎችን በትሕትና ማገልገል።

በክርስቶስ አካል ውስጥ አንድነትንና ትብብርን ማጠንከር።

ሁሉን በጸሎት መጀመርና በእግዚአብሔር ማመን።

ለእግዚአብሔር ፈቃድ ታዛዥ መሆን።

ለደካሞችና ለተቸገሩ ርኅራኄ ማሳየት።

በአገልግሎት ሁሉ በጥራትና በትጋት መሥራት።

ምስክርነቶችና ዜናዎች

ከመስኩ የተገኙ ምስክርነቶችና ወቅታዊ መረጃዎች።

እንኳን ወደ መልካም መንገድ በደህና መጡ

የመልካም መንገድ ዓለም አቀፍ የተልእኮ አገልግሎት ራእይ፣ ተልእኮና ጉዞ።

ምስክርነቱን ያንብቡ

ለተሰደዱ ጎን መቆም

በወንጌል ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ወንድሞችንና እህቶችን እንዴት እንደምንደግፍ።

ምስክርነቱን ያንብቡ

አገልግሎቱን ይደግፉ

የእርስዎ ልግስና አገልጋዮችን ያስታጥቃል፣ አብያተ ክርስቲያናትን ይተክላል፣ ስለ ወንጌል የሚሰቃዩ አማኞችን ይደግፋል።